ዜና አማራ ቻምበር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፍራ አባጆቢር ከተሠናባቹ ፕሬዚደንት መልአኩ እዘዘው (ኢንጅነር) የሥራ ርክክብ አደረጉ።
በርክክቡ ላይም፤ አቶ ሰብስብ አባፍራ ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረሥ የለውጥ ሥራዎችን ለመሥራት እና የተጀመሩ ሥራዎችን ግብ ለማድረሥ እንደሚተጉ ገልጸዋል።
ለንግዱ ማኀበረሠብ ድምጽ በመሆንና ከመንግሥት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን የሚወጣ ምክር ቤት እንዲሆን እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
ኢንጅነር መልእኩ እዘዘው በበኩላቸው አዲሱ ፕሬዚደንትና የሥራ አመራር ቦርድ ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንዲተጉ በማሣሠብ ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ ለማካፈልና አብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ባለፈው ሐምሌ 11/2016 በአፍሪካ ኀብረት ባካሄደው ሥብሠባ አቶ ሰብስብ አባፍራን ፕሬዚደንት፣ ዶክተር አይናለም አባይነሕን ምክትል ፕሬዚደንት እንዲሁም ዘጠኝ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን መምረጡ የሚታወስ ነው!
