ዜና አማራ ቻምበር
የአማራ ክልል የንግድናዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከጀርመኑ ሩትሊንገን ንግድናኢንዱስትሪ ም/ቤት በተገኘ የበጀት ድጋፍ በንግድ ምክር ቤት አባላት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው ከሀምሌ 5/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ቦኖሮያል ሆቴል የክልሉ ም/ቤትን ጨምሮ ከባህርዳር፤ከጎንደር፤ከደሴ እና ላሊበላ ም/ቤቶች የመጡ አመራሮች እና ሰራተኞች የስልጠናው ተሳታፊ ነበሩ፡፡
የአማራ ክልል የንግድናዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አሰፋ አላምረው ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት በዚህ ስልጠና የአባላትን መብት ፤ግዴታ፤ጥቅምና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማወቅ ወደፊት የተሻለ ስራ እንድንሰራ ስለሚያግዘን ትኩረት ሰጠን መከታተል ይገባናል ብለዋል ፡፡
በሌላ በኩል የስልጣው ተሳታፊዎችም ይህ ስልጠና በመዘጋጀቱ በማመስገን ለወደፊት የታሻለ ስራ ለመስራት ያግዘናል ብለዋል፡፡
